Wednesday, November 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜና‹‹ኢትዮጵያውያን 85 በመቶ ውኃቸውን አሳልፈው ሰጥተው በጨለማ ውስጥ የሚኖሩበት ምክንያት አይኖርም›› ...

‹‹ኢትዮጵያውያን 85 በመቶ ውኃቸውን አሳልፈው ሰጥተው በጨለማ ውስጥ የሚኖሩበት ምክንያት አይኖርም›› ጆ አሞች፣ የቀድሞ የናይሮቢ ከንቲባ

ቀን:

ኢትዮጵያውን 85 በመቶ የዓባይ ውኃ ባለቤት ሆነው ሳለ ለሌሎች አሳልፈው ሰጥተው በጨለማ ውስጥ የሚኖሩበት፣ ያለ ሥራ የሚቀመጡበትና መስኖ እንዳያለሙ የሚከለከሉበት ምንም ምክንያት ሊኖር አይችልም ሲሉ የኢትዮ ኬንያ ወንድማማቾች ማኅበር ሰብሳቢና የቀድሞው የናይሮቢ ከንቲባ ጆ አኬች ተናገሩ፡፡

ኢትዮጵያውን በራሳቸው ገንዘብና የገነቡትን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማንም መጥቶ ሊጠይቅ እንደማይገባ የተናገሩት የቀድሞው የናይሮቢ ከንቲባ፣ ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን እንዲያደርጉ ከሰው ፈቃድ መጠየቅ የለባቸውም ብለዋል፡፡

እሳቸው የተናገሩት የላይኛው ዓባይ ተፋሰስ አገሮች ፍትሐዊና ምክንያታዊ የውኃ አጠቃቀምን በተመለከተ ሰኞ ነሐሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በጀመረው የመጀመሪያው ከፍተኛ የትብብር ኮንፈረንስ ላይ ነው፡፡

የቀድሞው የናይሮቢ ከንቲባ እንደሚሉት የህዳሴ ግድብ ድርድርን በተመለከተ ግብፅና ሱዳን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ወደ አፍሪካ ኅብረት ሲልከው፣ የአፍሪካ ኅብረት ከጅምሩ ምን ይሠራ ነበር ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ግድብ የአውሮፓ ኅብረትንም ሆነ አሜሪካን የማይመለከት በመሆኑ፣ የአፍሪካ ኅብረት በጉዳዩ ላይ ዝምታውን አለመስበሩ ትክክል አይደለም ብለዋል፡፡

‹‹ጉዳዩ የተባበበሩት መንግሥታት ድርጅት በአፍሪካ ኅብረት እንዲታይ ከመራው በርካታ ወራት ሆኖት እስካሁን መዘግየት አልነበረበትም፣ በቶሎ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል የቀድሞው የሱዳን መስኖ ሚኒስቴር ኦስማን ኢልቶን (ዶ/ር)  በኢትዮጵያ ተራሮች ላይ የአፈር ጥበቃ በማድርግ፣ የውኃ ፍሰቱን ማሰተካከል እንደሚቻል፣ የዓባይ ተፋሰስ አገሮችም ትብብር ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ ‹‹እንደ አፍሪካ ራሳችን ከዓለም አቀፍ ዕርዳታና ዕይታ ነፃ ልናወጣ ይገባል፡፡ በአፍሪካ ላይ ያተኮሩ ጥናቶች ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ ከተፈለገ በራሳችን ልናከናውን ያስፈልጋል፤›› ብለዋል፡፡

ላላፉት አሥር ዓመታት የህዳሴ ግድቡን ሁኔታ በተመለከተ ሰባት የድርድር ሒደቶች እንደተካሄዱ የገለጹት ደግሞ የኢትዮጵያ የድርድር ኮሚቴ ሰብሳቢ ጌዲዮን አስፋው (ኢንጂነር) ናቸው፡፡ ‹‹የግድቡ ግንባታ ደረጃ 87.3 በመቶ ደርሷል፡፡ ከግብፅና ሱዳን ጋር ለሚደረገው ድርድር ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር የሴኔጋሉን ፕሬዚዳንት ጥሪ እየጠበቀች ናት፤›› በማለት ገልጸዋል፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር ሙሌት በነሐሴ ወር የተጠናቀቀ ሲሆን፣  ከሙሌቱ ጋር ተያይዞ የግድቡ ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...