Sunday, March 26, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ሁሉም የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከሕይወት መድን የሰበሰቡት ዓረቦን የ41 በመቶ ዕድገት አሳየ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ታሪክ በሕይወት የመድን ዋስትና (ኢንሹራንስ) ዘርፍ ለመጀመርያ ጊዜ በ2014 የሒሳብ ዓመት ከ1.4 ቢሊዮን ብር የዓረቦን ገቢ መገኘቱ ተገለጸ፡፡

እጅግ ዝቅተኛ አፈጻጸም የሚታይበት መሆኑ የሚጠቀሰው የሕይወት መድን ሽፋን በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት ከቀደሙት ዓመታት በተሻለ ዕድገት የታየበት አፈጻጸም በማስመዝገብ ሁሉም የአገሪቱ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከመድን ሽፋኑ ያሰባሰቡት የዓረቦን ገቢ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ ሪፖርተር ያገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡ 

የአገሪቱን የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ የ2014 የሥራ አፈጻጸም የሚያሳየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መረጃ ከሕይወት ኢንሹራንስ ዘርፍ የተሰበሰበው ዓረቦን ከቀዳሚው ዓመት የ41 በመቶ ብልጫ ማሳየቱንም ይጠቅሳል፡፡

18ቱም የአገሪቱ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በ2014 የሒሳብ ዓመት ካገኙት 16.7 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ የዓረቦን ገቢ ውስጥ ከሕይወት ኢንሹራንስ ዘርፉ የተሰበሰበው የዓረቦን መጠን 8.1 በመቶ ድርሻ መያዙንም ያመለክታል፡፡ 

ከዚህ ቀደም ከሕይወት ኢንሹራንስ ዘርፉ የሚሰበሰበው የዓረቦን ገቢ ከአጠቃላይ የዓረቦን ገቢ የነበረው ድርሻ በአማካይ የአምስት በመቶ የነበረው ሲሆን በ2014 የሒሳብ ዓመት ግን የ8.1 በመቶ ድርሻ ማበርከቱን መረጃው ያመለክታል።

የአገሪቱ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በ2014 የሒሳብ ዓመት ከሰበሰቡት አጠቃላይ 16.7 ቢሊዮን ብር የዓረቦን ገቢ ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነፃጸር የ24.3 በመቶ ዕድገት ያሳየ መሆኑንም መረጃ ያመለክታል፡፡ 

በሒሳብ ዓመቱ ሕይወት ነክ ካልሆነው የመድን ሽፋን የተሰበሰበው የዓረቦን ገቢ 15.3 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ዓመት ገቢ ጋር ሲነፃጸር የ18.6 በመቶ ዕድገት የታየበት ነው። በተጨማሪም ሕይወት ነክ ካልሆነ የመድን ሽፋን ዘርፍ የተገኘው የዓረቦን ገቢ የኢንሹራንስ ኩባንያዎቹ በአጠቃላይ ከሰበሰቡት ጠቅላላ የዓረቦን ገቢ ውስጥ 91.9 በመቶ ድርሻ የነበረው ሲሆን፣ ቀሪው 8.1 በመቶው ደግሞ ከሕይወት ኢንሹራንስ ዘርፍ የተሰበሰበ መሆኑን መረጃው ያመለክታል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች