ሆሄ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት፣ የሥነ ጽሑፍ ዘርፉን ወደ አንድ ዕርምጃ ከፍ ለማድረግና ለማበረታታት ዓላማ ያደረገ ድርጅት ነው፡፡ የልጆች መጻሕፍት፣ ግጥም፣ ረዥም ልብ ወለድ፣ የጥናትና ምርምርን ጨምሮ በስድስት ዘርፎች አወዳድሮም ይሸልማል፡፡
በዘንድሮ የሆሄ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት በ2011 ዓ.ም. የታተመ መጻሕፍትን አወዳድሮ ለመሸለም ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
በረዥም ልብ ወለድ አምስት፣ በልጆች መጻሕፍት ሦስት፣ በአጭር ልብ ወለደ ሦስት፣ በግጥም ሦስት፣ በግለ ታሪክ አምስት መጻሕፍትና በጥናትና ምርምር ስድስት መጻሕፍትን ለመሸለም ታጭቷል፡፡
ለአራተኛ ጊዜ የሚካሄደው የሆሄ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ነሐሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ምሽት በአዲስ አበባ የባህልና ቴአትር አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
በሁሉም ዘርፎች አንደኛ የሚወጡ መጽሐፍት የዓመቱ ምርጥ ተብለው ይሸለማሉ፡፡
ውጤቱ የሚመዘነው ከአንባቢያን 20 በመቶ እንዲሁም ድምፅና 80 በመቶ በዳኞች ግምገማ ነጥብ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡