የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በ2014 የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 1.3 ቢሊዮን ብር ማትረፉን አስታወቀ፡፡
በአገሪቱ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከፍተኛ የተባለውን ትርፍ ያስመዘገበው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የ2014 የሒሳብ ዓመት ትርፉ ከቀዳሚው ዓመት የ17.1 በመቶ ብልጫ አሳይቷል፡፡
ድርጅቱ ዛሬ ይፋ ባደረገው ሪፖርቱን በ2014 የሒሳብ ዓመት ያሰባሰበው የዓረቦን መጠን 6.5 ቢሊዮን ብር ነው፡፡
ይህም ከቀዳሚው ዓመት የዓረቦን ገቢው ጋር ሲነጻጸር የ7.3 በመቶ ወይም የ446 ሚሊዮን ብር ዕድገት ማሳየቱን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ነፃነት ለሜሳ ገልጸዋል፡፡