Saturday, March 25, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ትርፍ ለማግኘት አምስት ዓመታት ሊፈጅበት እንደሚችል አስታወቀ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በስድስት ሳምንታት ውስጥ አዲስ አበባ ላይ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል

በኢትዮያ ሁለተኛውን የቴሌኮም ፈቃድ በጨረታ አሸንፎ ሥራ የጀመረው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፣ ትርፍ ለማግኘት ቢያንስ አምስት ዓመታት ሊፈጅበት እንደሚችል አስታወቀ፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ በነዳጅ፣ በሲሚንቶና በሌሎች ግብዓች ላይ ዋጋ መጨመሩ ኩባንያው በቶሎ ትርፍ ለማግኘት እንቅፋት ሊሆንበት እንደሚችል የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለራሱ የመጀመሪያ የሆነውን የቴሌኮም አገልግሎት ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. በድሬዳዋ ከተማ በራሱ መሠረተ ልማት ማስጀመሩ ይታወቃል፡፡

ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ሲካሄድ የነበረው የመሠረተ ልማት ስምምነት በቶሎ ባለማጠናቀቁ አገልገሎቱን ለማስጀመር ጊዜ መውሰዱን የጠቀሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ በመጪዎቹ ስድስት ሳምንታት ወስጥ በተመሳሳይ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ እንዲሚያስጀምር አቶ አንዋር አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ባልቻ ሬባ (ኢንጂነር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ኩባንያው እስከ ሚያዚያ 2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያን 25 በመቶ የኅብረተሰብ ክፍል የሚሸፍን አገልግሎት እንዲያቀርብ ውል ገብቷል፡፡ ኩባንያው በዚሁ በተጠቀሰው ጊዜ የሚጠበቅበትን ካላሟላ ኦዲት ተደርጎ በገባው ውል መሠረት ቅጣት ይጣልበታል ብለዋል፡፡ ይሁን አንጂ የቴሌኮም ኩባንያው አሁን በተሳካ ሁኔታ ሥራውን እያከናወነ እንደሆነ ባልቻ (ኢንጂነር) ገልጸዋል፡፡

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንደሚሉት ኩባንያቸው የዋጋ ጦርነት ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ፈጣን የቴሌኮም አገልግሎት እንደሚያቀርብ አስረድተዋል፡፡

ከፍተኛ የሆነ ውድድር እንደሚጠብቃቸው የሚናገሩት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ኩባንያው የሚቀጥራቸው ሠራተኖች ባላቸው ብቃት፣ ለሚቀጠሩባቸው አካባቢዎች ያላቸው ግንዛቤና የቋንቋ ብቃት መሠረት ተደርጎ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በድሬዳዋ ከተማ የኔትወርክ ሙከራ በ2G፣ በ3G እና በ4G ኔትወርኮች የጀመረ ሲሆን፣ ደንበኞች በ07 በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮቻቸውን መርጠው ሲም ካርድ መግዛት እንደሚችሉ ኩባንያው አስታውቋል፡፡

በድሬዳዋ ከተማ አገልግሎት በጀመረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ ደንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎችና የጽሑፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ፣ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ ሳፋሪኮም በደቂቃ 50 ሳንቲም እንደሚያስከፍልም ታውቋል፡፡

የመጀመሪያው የግል የቴሌኮም ኦፕሬተር ሆኖ በኢትዮጵያ የተመዘገበው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ላገኘው የአገልግሎት ፈቃድ 850 ሚሊዮን ዶላር ለመንግሥት መክፈሉ ይታወሳል፡፡ በቀጣዮቹ አሥር ዓመታት 8.5 ቢሊዮን ዶላር ገደማ በዘርፉ ፈሰስ በማድረግ አዳዲስ አገልግሎቶችንና መሠረተ ልማቶችን እንደሚያቀርብ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች