መንግሥት ይህን ያለው ለህወሃት ፀረ ሰላም ዕብሪት ምንጭ የሆኑ ወታደራዊ ዐቅሞችን ዒላማ ያደረገ እርምጃ እንደሚወስድ በገለፀበት ወቅት ነው፡፡
መንግሥት እስከ አሁን ድረስ ለሰላም በሩን ክፍት አድርጎ ቢጠባበቅም ህዉሃት ጥቃቱን ቀጥሎበታል ያለው የመንግስት መግጫ ፣ የፌዴራል መንግሥት ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር የገለጸው ዝግጁነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለህዉሃት ፀረ ሰላም ዕብሪት ምንጭ የሆኑ የተመረጡ ወታደራዊ ዐቅሞችን ዒላማ ያደረገ እርምጃ እደሚወስድ አስታውቋል።
“ስለሆነም በትግራይ የምትኖሩ ወገኖቻችን በተለይም የህወሃት ወታደራዊ መሣሪያዎች እና ማሠልጠኛዎች ካሉባቸው አካባቢዎች ራሳችሁን እንድታርቁ ይመከራል” ሲል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን በመግለጫው አሳስቧል፡፡