Tuesday, March 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበኦጋዴን ቤዚን ሰባት ትሪሊየን ኪዩቢክ ጫማ የተፈጥሮ ነዳጅ ክምችት መኖሩ ተረጋገጠ

በኦጋዴን ቤዚን ሰባት ትሪሊየን ኪዩቢክ ጫማ የተፈጥሮ ነዳጅ ክምችት መኖሩ ተረጋገጠ

ቀን:

በኢትዮጵያ ደቡብ ምስራቅ ክፍል ኦጋዴን ቤዚን ያለው የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ሰባት ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ መሆኑ በጥናት መረጋገጡን የማዕድን ሚኒስቴር ኢንጅነር ታከለ ኡማ አስታወቁ፡፡
 
በኦጋዴን ቤዚን ያለውን ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት ክምችትና የኢኮኖሚ አዋጭነት ጥናት ለማድረግ መጋቢት 2014 ዓ.ም. ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር ውል የገባው የአሜሪካው ኔዘርላንድ ስዌል ኤንድ አሶሲሼየትስ ኢንክ ኩባንያ የጥናቱን ሰነድ ዛሬ አርብ ነሐሴ 20፣ 2014 ዓ.ም. ለሚኒስቴሩ አስረክቧል፡፡
 
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነው በተባለለት በዚህ ጥናት ከዚህ ቀደም ከሁለት እስከ ሶስት ትሪሊየን ኪዩቢክ ጫማ እንደሆነ ሲገመት የነበረው የኦጋዴን ቤዚን የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት በሁለትና ሶስት እጥፍ የጨመረ ሆኖ መገኘቱን ኢንጅነር ታከለ ተናግረዋል፡፡
 
“ከዚህ ቀደም የነበሩ ኩባንዎች ምን ያህል ክምችት እንዳለ አይነግሩንም ነበር” ያሉት ሚኒስትሩ አሁን የተጠናው ጥናት ግን ለክምችቱ መጠን ዓለም አቀፍ ማረጋገጫ መስጠቱን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ስለክምችቱ የነበሩ ጥናቶች የኩባንያዎች እንደሆኑ አሁን በአሜሪካው ኩባንያ የተደረገው ጥናት ግን የመንግስት መሆኑን ኢንጅነር ታከለ አክለዋል፡፡
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹ከኦነግ ሸኔ ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት አለን›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ

መንግሥት ከ‹‹ኦነግ ሸኔ››ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት...

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...