Tuesday, March 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየኢትዮጵያን የአየር ክልል ጥሶ ወደ ትግራይ ክልል ሊገባ የነበረ የጦር መሳሪያ የጫነ...

የኢትዮጵያን የአየር ክልል ጥሶ ወደ ትግራይ ክልል ሊገባ የነበረ የጦር መሳሪያ የጫነ አዉሮፕላን መመታቱ ተገለጸ፡፡

ቀን:

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መከላከያን ጠቅሰው በትዊተር ገፃቸው ይፋ እንዳደረጉት፣ በሱዳን አድርጎ የኢትዮጵያን አየር ክልል ጥሶ በሁመራ ሰሜናዊ ክፍል በኩል ወደ ትግራይ ሊያልፍ የነበረና ለህውሃት የጦር መሳሪያ ሊያቀበል የነበረ ማንንቱ ያልታወቀ አውሮፕላን በአየር ሃይል ትናንት ሌሊት ተመትቶ ወድቋል፡፡

በሀገር መከላከያ ሠራዊት የመከላከያ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊ ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው በበኩላቸው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስደፈር የሽብር ቡድኑን እየጋለቡ ያሉ ሃይሎች እንዳሉ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን ገልፀዋል፡፡

ይሁን እንጅ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ለማስከበር በተጠንቀቅ ላይ መሆናቸውን ሜጀር ጀነራሉ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም የሽብር ቡድኑ ሀገር የማፍረስ ህልሙን ትቶ ወደ ሰላማዊ መፍትሔ ካልመጣ እስከ መጨረሻው እርምጃ ለመውሰድ ሙሉ ዝግጅት መደረጉን ሜጀር ጀነራሉ አስታዉቋል፡፡

ላለፉት በርካታ ወራት ከፍተኛ ወታደራዊ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው አሸባሪው ህወሃት ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ኃይሉን ለውጊያ ሲያስጠጋ ነበር ተብሏል።

ህወሓት በበኩሉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ መከላከያ ሰራዊትና የአማራ ክልል ልዩ ኃይል በትግራይ ደቡባዊ አቅጣጫ ባለው ግንባር በኩል ተኩስ ከፍተውብኛል ሲል አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹ከኦነግ ሸኔ ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት አለን›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ

መንግሥት ከ‹‹ኦነግ ሸኔ››ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት...

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...