Wednesday, October 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ አማካሪያቸው ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ሳለ አማካሪያቸው ባነሳው አንድ ጥያቄ ተበሳጩ]

  • ክቡር ሚኒስትር፣ እንዲያው ይቅርታ ያድርጉልኝና አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎት እችላለሁ?
  • ምን ዓይነት ጥያቄ ቢሆን ነው? ለማንኛውም ጠይቀኝ ችግር የለውም። 
  • በእርስዎ እምነት ገዥው ፓርቲ ከሠራቸው ስኬታማ ሥራዎች ግንባር ቀደም የሚሉት ምንድነው? 
  • ከባድ ጥያቄ ነው፡፡
  • እንዴት? 
  • ምክንያቱም ለማበላለጥ ይከብዳል፣ ከወለድካቸው ልጆችህ ወይም ከእጅህ ጣቶች መካከል የቱን አስበልጠህ ትወዳለህ እንደ ማለት ነው፣ ለእኔ ሁሉም ስኬቶች እኩል ናቸው ማለት ይቀለኛል።
  • አርቲስት ነው የመሰሉኝ ክቡር ሚኒስትር። 
  • እንዴት? 
  • እነሱ ናቸው ብዙ ጊዜ እንዲህ ዓይነት መልስ የሚሰጡት፣ በተለይ በሚዲያ በሚተላለፉ የበዓል ፕሮግራሞች ላይ።
  • ለመሆኑ ለምንድነው የጠየቅከኝ? ልትነግረኝ የፈለግከው ነገር አለ? 
  • እንደዚያ ሳይሆን ነገሩ ቢያስገርመኝ ነው እርስዎን መጠየቅ የፈለግኩት። 
  • ያስገረመህ ነገር ምንድነው? 
  • ገዥው ፓርቲ ከሠራቸው ሁሉ የሚበልጠው ትልቁ ነገር የአስተዳደር ወሰኑን ማካለሉ ነው መባሉ።
  • ለምን አስገረመህ? 
  • ትልቅ ነገር አይደለማ፡፡ 
  • እንዴት? ለምን?
  • ጥያቄውን ያነሳነው እኛው ነን፣ ለፖለቲካ ትግል ብለን ራሳችን ያነሳነውን ጥያቄ ሥልጣን ላይ ወጥተን መልስ መስጠታችን ተዓምር አይደለም ብዬ ነው። 
  • ጅል፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር እየሰደቡኝ ነው?
  • ስድብ አይደለም።
  • ጅል አሉኝ እኮ?
  • ስድብ አይደለም ስልህ፡፡
  • ታዲያ ምን ማለት ነው?
  • እንደ ፓርቲ አባል ሳይሆን አንደ ማኅበረሰብ አንቂ ወይም አክቲቪስት ነው የጠየቅከው ለማለት ነው፣ እነሱ ናቸው የነቁ መስሏቸው እንዲህ ዓይነት ጥያቄ የሚያነሱት።
  • በእርግጥ ይህኑኑ ጥያቄ አንዳንድ ታዋቂ ሰዎች በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ሲያነሱ ተመልክቻለሁ ቢሆንም ተገቢ ጥያቄ ይመስለኛል።
  • ጅላ ጅል፡፡
  • ጅላ ጅል አሉኝ ክቡር ሚኒስትር? ጆሮዬ መሆን አለበት፡፡ 
  • ጆሮህ አይደለም፡፡ 
  • እና ምን አጠፍቼ ነው የሰደቡኝ ታዲያ? 
  • ስድብ አይደለም፡፡
  • ጅላ ጅል ስድብ ካልሆነ ምን ሊሆን ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • ለራሳቸው ሳይነቁ ማኅበረሰብ አንቂ ነን የሚሉ ጅል ናቸው አላልኩህም? 
  • ባልስማማበትም ብለውኛል። 
  • አዲሱ ዕይታችን ነው፣ የአንተ መስማማት አስፈላጊ አይደለም። 
  • እሺ… ምን ይደረጋል… ይሁን፣ ስለዚህ ጅላ ጅል ማለት ምን ማለት ነው?
  • ጅሎችንና ሐሳባቸውን ለሚከተሉ የተሰጠ ስያሜ ነው። 
  • በአዲሱ የድርጅታችን ዕይታ ማለት ነው? 
  • አዎ፣ ልክ ነው፡፡ 
  • እኔ የምልዎት ክቡር ሚኒስትር?
  • እህ…
  • ሐሳቦችን ለመፈረጅ ጊዜ ከምናጠፋ ጥያቄዎችን ብንመልስ አይሻልም? 
  • አሁን ደግሞ ምን እንደምትባል ታውቃለህ?
  • ምን እባላለሁ?
  • ጅላንፎ! 

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከአንድ አብሮ አደግ ወዳጃቸው ጋር በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ስለአገር ጉዳይ እየተጨዋወቱ የዕረፍት ቀናቸውን እያሳለፉ ነው] 

  • እኔ ምልህ ክቡር ሚኒስትር?
  • እንዲያው ይኼን ክቡር ሚኒስትር ማለት ተወኝ አላልኩህም?
  • አንተ ባትፈልግም ለተቋሙ ክብር መንፈግ ባህላችን አይደለም፣ ይልቅ ልጠይቅህ የነበረውን አስረሳኸኝ፡፡
  • ምን ልትጠይቅ ነበር?
  • አዎ፣ አስታወስኩት፣ እኔ የምልህ?
  • እህ…
  • መንግሥት በተደጋጋሚ ጊዜ ለሰላም ዝግጁ ነኝ እያለ በይፋ እየገለጸ ነው። አይደለም?
  • ትክክል ነው እሱማ፣ እነሱም ሰላም እንፈልጋለን ይላሉ፡፡ ታዲያ ሰላም ማውረድ ለምን አልተቻለም? ችግሩ ምንድነው?
  • ግራ ተጋብተው ግራ እያጋቡን መሆኑ ነው ችግሩ።
  • እንዴት? 
  • ሰላም እንፈልጋለን ይላሉ፣ ግን ደግሞ ግራ የሚያጋባ ቅደመ ሁኔታ ያስቀምጣሉ።
  • ምንድነው ግራ የሚያጋባው ቅድመ ሁኔታ? 
  • ለሰላም ዝግጁ ከሆናችሁ በቅድሚያ መግባት አለባችሁ ይሉናል፡፡ 
  • መግባት አለባችሁ ይሉናል ነው ያልከው ክቡር ሚኒስትር? 
  • አዎ።
  • ወዴት?
  • እነሱ ወደ የሚያስተዳድሩት ክልል። 
  • ለምን? ምን እንድታደርጉ ነው?
  • ቴሌ፣ ባንክና ሌሎች አገልግሎቶችን እንድንጀምር። 
  • አገልግሎት ለማግኘት ብለው ነዋ፡፡
  • አዎ፣ ግን ደግሞ ንግድ ባንክም ሆነ ቴሌ የፌዴራል መንግሥት ተቋማት ናቸው።
  • እሱማ ልክ ነው፣ በተጨማሪም የፌዴራል መንግሥት በየትኛውም አካባቢ የመሰማራት መብት አለው። 
  • አሱን ተወውና ያነሱትን ጥያቄ ተቀብለን ለመግባት ስንዘጋጅ ደግሞ ውጡ ይሉናል። 
  • ከየት? ገና ሳትገቡ?
  • ከምዕራቡ ወሰን ውጡ ይሉናል።
  • ሠራዊቱን ማለታቸው ነዋ፡፡
  • አንተ ራስህ የፌዴራል መንግሥት በየትኛውም አካባቢ መሰማራት ይችላል ስትል አልነበር እንዴ?
  • በእርግጥ ብያለሁ። 
  • ታዲያ የፌዴራል መንግሥቱን ሠራዊት ለምን ይውጣ ይላሉ?
  • ተመልከት አንዴ ሠራዊቱ ይውጣ ይሉናል፣ እዚያው ደግሞ አገልግሎት ሰጪ የፌዴራል ተቋማት ካልገቡ ይሉናል።
  • በመግለጫችሁ ላይ በኋላ ያላችሁት ነገር አሁን ነው የገባኝ፡፡
  • በኋላ ያልነው ምንድነው? 
  • መግባትና መውጣት! 

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅን የሚተካ ረቂቅ ተዘጋጀ

  ከቫት ነፃ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ገደብ ተቀመጠለት የገንዘብ ሚኒስቴር ከሃያ...

  የአገር ውስጥ የፍራፍሬ ገበያን ፍላጎት ይሸፍናል የተባለለት የብላቴው እርሻ ልማት

  መንግሥት የግብርና ምርታማነትና የፍራፍሬ ምርትን ለማሳደግ በ‹‹አረንጓዴ አሻራ›› በሚል...

  ባንኮች እንዲዋሀዱ እስከ ማስገደድ ሊገባ እንደሚችል ብሔራዊ ባንክ ጠቆመ

  በአሁኑ ወቅት የባንኮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ችግር የሚሆንና የውጭ...

  ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ በርካታ ሰዎች ወደ ከተማዋ እንዳይገቡ በፖሊስ መከልከላቸውን ገለጹ

  ‹‹የኦሮሚያ ክልል መፍትሔ እንዲሰጥበት አሳውቀናል›› የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ‹‹ጉዳዩ...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  የአፍሪካ ሕብረት የሰላም ንግግሩን ለማስጀመር ያቀረበውን ጥሪ መንግስት ተቀበለ

  የአፍሪካ ሕብረት በፌደራል መንግስትና በህወሃት መካከል የሰላም ንግግር እንዲጀመር...