Tuesday, March 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ፍሬከናፍር‹‹ደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ውዝግብ ለመፍታት የሚያስችል ውይይት ለማዘጋጀት ፈቃደኛ ናት››

‹‹ደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ውዝግብ ለመፍታት የሚያስችል ውይይት ለማዘጋጀት ፈቃደኛ ናት››

ቀን:

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ብሔራዊ የደኅንነት አማካሪ ቱት ጋትሉክ ሚናሜ፣ ሰሞኑን በሱዳን በነበራቸው ጉብኝት ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፡፡ የደኅንነት አማካሪው ከሱዳን ጊዜያዊ ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ጋር በሁለቱ አገሮች የፖለቲካና የድንበር ጉዳዮች ላይ በተወያዩበት ወቅት፣ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ከኢትዮጵያና ከሱዳን መሪዎች ጋር የሦስትዮሽ ውይይት የሚደረግበት ስብሰባ በማዘጋጀት የድንበር ውዝግቡን ለመፍታት ዕቅድ እንዳላቸው እንደ ነገሯቸው ዢኑዋ ከካርቱም ዘግቧል፡፡ ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር ጥሳ ገብታ ሰፋ ያለ መሬት በወረራ በመያዟ ምክንያት፣ በሁለቱ አገሮች መካከል መቃቃር መፈጠሩ ይታወሳል፡፡ በተለይ ኢትዮጵያ ችግሩ በዲፕሎማሲ ተፈቶ የሁለቱ አገሮች ወዳጅነት ወደ ነበረበት እንዲመለስ በተደጋጋሚ ማስታወቋ አይዘነጋም፡፡ በምሥሉ ላይ የሚታዩት የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹ከኦነግ ሸኔ ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት አለን›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ

መንግሥት ከ‹‹ኦነግ ሸኔ››ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት...

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...