Saturday, March 25, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊዩኤስኤይድ ለአደጋ ዝግጁነት ሥልጠና ከሰባት ሚሊዮን ዶላር በላይ የድጋፍ ስምምነት አደረገ

ዩኤስኤይድ ለአደጋ ዝግጁነት ሥልጠና ከሰባት ሚሊዮን ዶላር በላይ የድጋፍ ስምምነት አደረገ

ቀን:

የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሚስተር ሲያን ጆንስ ድርጅታቸው በአማራ ክልል ለሚገኙ 750 የአደጋ ዝግጁነት ባለሙያዎች ሥልጠና የሚውል የ7.7 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ስምምነት ማድረጋቸው ተገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ሐምሌ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ይህንኑ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ ሥልጠናው የሚካሄደው በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሲሆን፣ ይህ ዓይነቱም ድጋፍ በዩኒቨርሲቲው ታሪክ ትልቁና የመጀመርያው ነው፡፡

አሜሪካ ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ጊዜ እያካሄደ ላለው የአደጋ ዝግጁነትና የምግብ ዋስትና ጥናት ጨምሮ ለልዩ ልዩ ሥራዎችን ማከናወኛ የገንዘብ ድጋፍ ስታደርግ ሁለት አሥርተ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

የድርጀቱ ዳይሬክተር ከዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ተስፋዬ ሺፈራው (ዶ/ር) ከባህር ዳር ከተማ ከንቲባ ደረሰ ሳህሉ (ዶ/ር)፣ ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ መልካሙ አባተ (ዶ/ር) ጋር በየተራ ተገናኝተው እንደተነጋገሩ መግለጫው አመላክቷል፡፡

ሚስተር ሲያን ጆንስ ስምንት የሞተር ሳይክሎችን ለከንቲባው ማስረከባቸውን፣ ሞተር ሳይክሎቹ ልዩ ልዩ መድኃኒቶችንና የሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶችን ወደየጤና ተቋማቱ እንደሚያጓጉዙ ለሐኪሞችና ለሌሎችም የጤና ባለሙያዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡

ሚስተር ሲያን ጆንስ ከአማራ ልማትና ማቋቋሚያ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓለማየሁ ዋሴ፣ ከድርጅቱ አጋሮችና ከተፈናቃዮች ተጠሪዎች ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን መግለጫው አስፍሯል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ በመላ ኢትዮጵያ ለሚካሄደው ሰብዓዊ ዕርዳታ ልማት በ2021 ብቻ 1.2 ቢሊዮን ዶላር ዕርዳታ ማድረጓን፣ በተለይ በአማራ ክልል ብቻ ባለፉት ሁለት ዓመታት 430 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የሰብዓዊና የልማት ዕርዳታ ማበርከቷንም አስፍሯል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኩባንያ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ባንኮች ውጤታማነት

የጠቅላላ ጉባኤ፣ የጥቆማና ምርጫ ኮሚቴ፣ የተቆጣጣሪ ቦርድ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...