Tuesday, March 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልቡሄ መጣ ያ መላጣ

ቡሄ መጣ ያ መላጣ

ቀን:

ቡሄ በየዓመቱ የሚከበር የልጆች በዓል ነው፤ ልጆች ክረምቱን ከትምህርት እረፍት ስለሚሆኑ ቡሄን ለመጨፈር ይናፍቃሉ፡፡ በዓሉ የሚውለው ነሐሴ 13 ቀን ነው፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ቀኑ ደብረ ታቦር ተብሎ ይጠራል፡፡ በዓሉ በልጆች የሚደምቅ ቢሆንም፣ ልክ እንደ ፋሲካና ገና የዋዜማው ሌሊት በቤተ ክርስቲያን በዝማሬ፣ በማህሌትና በፀሎት የሚከበርበት ነው፡፡ በደብር በሃይማኖታዊ ሥርዓት በመንደር ደግሞ በባህላዊ ሥርዓት ይከበራል፡፡

የአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ቡሄ የሚለውን ቃል ቡሐዊ የበዓል ስም ደብረታቦር፣ ቡሄ ብርሃን ብርሃናዊ ብርሃኔ መብራቴ ችቦዬ ዳቦቴ በሚል ይፈታዋል፡፡

በዕለቱ የታቦር ቀን በነሐሴ 13 የሚጋገረው ኅብስት ዳቦ፣ ሙልሙልም ቡሄ ተብሎ እንደሚጠራ የኪዳነወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ያስረዳል፡፡ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚከበረው ቡሄ በአንዳንድ አካባቢዎች በዋዜማው በተወሰኑ አካባቢዎች ደግሞ በዕለቱ ነሐሴ 13 ቀን  ችቦ ተለኩሶ ጎረቤት ተሰብስቦ ልጆች እየጨፈሩ ምሽት ላይ ያከብሩታል፣ ይመራረቁበታል፡፡ቡሄ መጣ ያ መላጣ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

በገጠር ከቡሄ ጭፈራው በተጨማሪ ጅራፍ እየገመዱ ያስጮሃሉ፣ ወጣቶችም እርስ በርስ በጅራፍ ተመራርጠው ይገራረፋሉ፣ በጅራፉ የተሸነፈው ወገን ሸሽቶ መሸነፉን ይገልጻል፡፡ በአንዳንድ ቦታዎች ደግሞ ሲገራረፉ አባቶች እንደ ዳኛ ቁጭ ብለው ያያሉ፣ አሸናፊውን ይለያሉ፡፡

የሚገራረፉት ከወገብ በታች ያለውን የሰውነት ክፍል ነው፡፡ በከተሞች ጅራፍ ከማስጮህ ውጪ መገራረፍ የሚባለው ነገር አይታወቅም፡፡ በጅራፍ መገራረፍ ከሸዋ እስከ ደቡብ ትግራይ የሚታይ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ቡሄ፣ መላጣ ገላጣ ማለት ነው ይላሉ፣ በቡሄ ጭፈራ ሕፃናት ሲዘፍኑትም

ቡሄ መጣ
ያ መላጣ
ቂቤ ቀቡት

እንዳይነጣ

የሚሉት ለዚህ ነው፡፡ በገጠራማ አካባቢዎች በቡሄ ዕለት የተላጨ የተመለጠ ፀጉር አያበቅልም ተብሎ ስለሚታሰብ የልጃቸውን መላጣ ያላቸው ቅቤ ይቀቡታል፣ የሌላቸው ደግሞ በአጓት መላጣውን ያጥቡት ነበር፡፡

መጣና በዓመቱ
እንደምን ሰነበቱ
ቡሄ በሉ ልጆች ሁሉ
ሆያ ሆዬ
እዚያ ማዶ ጭስ ይጨሳል
አጋፋሪ ይደግሳል
ያቺን ድግስ ውጬ ውጬ
በድንክ አልጋ ተገልብጬ
ያቺ ደንክ አልጋ አመለኛ
አለ አንድ ሰው አታስተኛ
እዚያ ማዶ ሆ አለኝ ለከት
እዚህ ማዶ አለኝ ለከት
ተከምሯል እንደኩበት ይላሉ፡፡ (ለከት ከስንዴ ዱቄት የተጋገረ ሞላላ ዳቦ በአንዳንድ ቦታዎች ጥቢኛ በሚባል የሚጠራ ነው፡፡)
የኔማ ጌታ የሰጠኝ ሙክት
በግንባሩ ላይ አለው ምልክት
የኔማ እመቤት አትውጪ ጓሮ
ገላሽ ያበራል እንደ ቆርቆሮ ….

እያሉ ይጨፍራሉ፡፡ ሲጨፍሩ እንደ አካባቢው ነው፡፡ በገጠር ሙልሙል ዳቦ ይሰጣቸዋል፡፡ በከተሞች ገንዘብ ይሰጣቸዋል፡፡          

ወንዜ ነበረ

የወንዜ ነበረ

ሊሰጡን ነበረ ሳይመነዘረ

የዚህ ጽሑፍ ባለቤት ኃይለማርያም ወንድሙ (2012 ዓ.ም.) እንዳስቀመጡት፣
‹‹እኛም እንደ ወጉ በልጅነታችን የተለያዩ አካባቢዎች ሄደን ጨፍረን ገንዘብ ሰብስበን እንከፋፈል ነበር፡፡ በመርካቶ ንግድ ቦታዎች ሄደን ስንጨፍር ሁላችን በኪሳችን ጠንከር ያለ ፌስታል ይዘን ሄደን ነበር፡፡ ከገንዘብ ይልቅ ቁሳቁስ የሚሰጡን ስላሉ፡፡ የምንጨፍረው በፕሮግራም ነው፡፡ ግማሹን ሰዓት ሽንኩርት ተራና መርካቶ አትክልት ተራ (ከአመዴ ገበያ ወረድ ብሎ የነበረ ቦታ) ስንጨፍር፣ ቃሪያ፣ ሽንኩርት፣ ቲማቲም ድንች ይሰጠናል፡፡ በርከት ሲልና ለመያዝ ስንቸገር ጭፈራችን ገታ አድርገን ለሸማቾች በርካሽ ዋጋ እንሸጥ ነበር፡፡

ኃይለማርያም ወንድሙ (2012)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹ከኦነግ ሸኔ ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት አለን›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ

መንግሥት ከ‹‹ኦነግ ሸኔ››ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት...

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...