Saturday, March 25, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅእንግጫ ነቀላ

እንግጫ ነቀላ

ቀን:

በምሥራቅ ጎጃም ዞን በወርሐ ነሐሴና ጳጉሜን የሚከወኑ በርካታ የማይዳሰሱ ባህላዊ ክዋኔዎች አሉ። ከእነዚህ ባህላዊ ሀብቶች መካከል ቡሄ፣ አሸንድየ፣ ከሴ አጨዳ፣ እንግጫ ነቀላና በዓባይ ወንዝ ላይ የሚከበረው የዓባይ ሩፋኤል ይገኙበታል፡፡ በእነዚህ በዓላት በአብዛኛው ሕፃናት፣ ወጣቶችና ልጃገረዶች የሚሳተፉባቸው ናቸው፡፡ የእነሱ የመጫወቻ፣ የመደሰቻ፣ የማመስገኛና የነፃነት ጊዜያትም ናቸው፡፡ እነዚህን ባህላዊ ሀብቶች የጎጃም ማኅበረሰብ ከቀደመው ትውልድ ተረክቦ፣ ጠብቆና ተንከባክቦ አቆይቷል፡፡ በአዲሱ ትውልድ ግን እየተረሱና እየደበዘዙ የመጡ በዓላት ናቸው፡፡ ሆኖም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የአማራ ክልል ባህላዊ ሀብቶችን በማስተዋወቅና የቱሪዝም ሀብትነታቸውን ለማሳደግ እየሠራ ይገኛል፡፡ በዚህ ወቅት የሚከበረውን እንግጫ ነቀላ፣ አሸንድዬና ከሴ አጨዳ አስመልክቶም ግንዛቤ እየሰጠ ይገኛል፡፡ እንግጫ የሳር ዓይነት ነው፡፡ የእንግጫ ነቀላ በዓል ደግሞ ዘመን ሲለወጥ  የሚከወን ባህላዊ ሥርዓት ነው፡፡ በአዲስ ዓመት ዋዜማ ልጃገረዶች  ወንዝ ወርደው እንግጫ ይቆርጣሉ፡፡ በዚያው ቀን ማምሻ  የቆረጡትን እንግጫ ይጎነጉኑታል፡፡ ሲነጋ ልጃገረዶቹ ከያሉበት ተጠራርተው በመሰባሰብ  በየሰው ቤት እየዞሩ የተጎነጎነውን እንግጫ የቤቱ ምሰሶ ላይ በማሰር አዲሱን ዓመት ያበስራሉ፡፡ ይህ ባህላዊ ክዋኔ በዜማና በጭፈራ የታጀበ ነው፡፡   

ነሐሴ አጋማሹና ጳጉሜን በጎጃም ምድሩ በልምላሜ ተውቦ ሕፃናት፣ ወጣቶችና ልጃገረዶች እነዚህን ባህላዊ ክዋኔዎች ሲጫወቱ ማየት የተለመደ ነው፡፡

እነዚህን ባህላዊ ሀብቶች በማልማት የማኅበረሰቡ መገለጫና መታወቂያ ለማድረግና ለቱሪስት መስህብነት ለማዋል ከ2009 ዓ.ም. ጀምሮ በየወረዳው በዓሉ ከተከበረ በኋላ እንደ ዞን ደግሞ ደብረ ማርቆስ ላይ ማክበር መጀመሩ ይታወሳል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት በኮቪድና በህልውና ዘመቻው ምክንያት በዓሉን እንደወትሮው በአደባባይ ደምቆ ባይከበርም፣ በደም ልገሳና በተለያዩ ማኅበራዊ ተግባራት እንደተከናወነ የአማራ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያሳያል፡፡

ዘንድሮ ከጳጉሜን 1 እስከ ጳጉሜን 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ደብረ ማርቆስ ላይ በመስክ ሙሉ የእንግጫ ነቀላ ባህላዊ ክዋኔውን በማሳየት፣ በንጉሥ ተክለ ሃይማኖት አደባባይ የእንግጫ ነቀላን ታሪክ የሚያሳይ ፓናል ውይይት፣ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ በፎቶና ዕደ ጥበባት ኤግዚቢሽንና ሌሎችም ዝግጅቶች የሚከበር ይሆናል፡፡

እንግጫ ነቀላ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

እንግጫ ነቀላ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

(ፎቶ የአማራ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኩባንያ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ባንኮች ውጤታማነት

የጠቅላላ ጉባኤ፣ የጥቆማና ምርጫ ኮሚቴ፣ የተቆጣጣሪ ቦርድ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...