Wednesday, October 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ፍሬከናፍር‹‹ኬንያውያን ወገኖቼ በሕይወቴ ታላቅ ለሚባል ክብር ስላበቃችሁኝ አመሠግናለሁ››

  ‹‹ኬንያውያን ወገኖቼ በሕይወቴ ታላቅ ለሚባል ክብር ስላበቃችሁኝ አመሠግናለሁ››

  ቀን:

  በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ሰኞ ነሐሴ 9 ቀን 2014 ዓ.ም. አሸናፊነታቸው በኬንያ የድንበርና የምርጫ ኮሚሽን ሊቀመንበር ይፋ የተደረገው አዲሱ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሳሞይ ሩቶ በትዊተር ገጻቸው ካሠፈሩት የተወሰደ፡፡ ተፎካካሪዎቹን በጠባብ ልዩነት በለየው ምርጫ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ከአጠቃላይ መራጮች 50.5 በመቶ በማግኘት ማሸነፋቸው ሲገለጽ፣ ለአምስት ጊዜያት ያህል ለፕሬዚዳንትነት ቢፎካከሩም አሁንም አልቀናቸውም የተባሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ 48.8 በመቶ በማግኘት ተሸንፈዋል ተብሏል፡፡ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ሁሉንም ኬንያውያን በእኩልነት እንደሚያገለግሉ አስታውቀው፣ ‹‹በእኛ ላይ በርካታ አሉታዊ ድርጊቶችን የፈጸሙ በፍፁም ፍራቻ አይሰማቸው፡፡ በቀል የሚባል ነገር የለም፡፡ ወደ ኋላ ለመመልከት የሚያስችል ቅንጦት የለንም፤›› ብለዋል፡፡ የራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች ውጤቱን በመቃወም ተቃውሞ ቢያሰሙም፣ ከተለያዩ አካላት የተውጣጡ ኬንያውያን የሚሳተፉበት የገለልተኛ ታዛቢዎች ቡድን ውጤቱ ከድምፅ ቆጠራው ጋር የተናበበ ነው ማለቱ ተዘግቧል፡፡ በምሥሉ ላይ የሚታዩት ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ናቸው፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img