Wednesday, October 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዝንቅ  በብርድ ለምትኖሩ

    በብርድ ለምትኖሩ

  ቀን:

  ጉም ጭጋግ ለብሳችሁ

  ለሰማይ ቀርባችሁ፤

  ካምላክ ጉርብትና ወሰን ተጋርታችሁ፤

  እደጋማው ሃገር በከፍታው ምድር፣ ርቃችሁ ያላችሁ፡፡

  የምድጃችሁ ፍም የማያንቀላፋ

  የመንደራችሁ ጢስ ዘወትር የማይጠፋ

  ተራሮች አናት ላይ በብርድ የምትኖሩ፣

       የደጋ

       ደግ ሰዎች

  በጋው ሣይገሰግስ

       ፀሐይ ሣትጨፈግግ

        ቁሩ ሣይጠነክር

               ክረምቱ ሣይመጣ

                     ይህን ሥራ ሥሩ፡፡

                  ***

  አጋሰስ መጋዣ በሮች እስክትመስሉ፤

        ከጋጣው አትራቁ  

         ከበረት አትጥፉ

         ከከብቶች ስር ዋሉ፡፡

  ተዳፋት ሜዳውን ገለባ አንጥፉ

  አዛባውን ዛቁ እበቱን ጠፍጥፉ

  ፋንድያን አድርቁ በተገኘው ስፍራ

  ኩበቱን ከምሩ እስኪመስል ተራራ

  ሣይቸግር ጭራሮ ክረምቱ ሣይመጣ

  ደረቅ እንጨት ባገር ፍፁም ሣይታጣ

  የክፉ ቀን ቤዛ

      ኩበት እንዲበዛ

  የክፉ ቀን ቤዛ

       ፋንድያ ንዲበዛ

  ተራሮች አናት ላይ በብርድ የምትኖሩ

       የደጋ ደግ ሰዎች

       (እንዲህ እንዲህ) ይህን ሥራ ሥሩ፡፡ 

                  ***

  ጉም ጭጋግ ለብሣችሁ

  ለሰማይ ቀርባችሁ

  ከፈጣሪ ወሰን ድንበር ተጋርታችሁ

  እደጋማ ሃገር በከፍታው ምድር ርቃችሁ ያላችሁ

  የምድጃችሁ ፍም እንዳያንቀላፋ የመንደራችሁ ጢስ ዘወትር ንዳይጠፋ፡፡

         ፅኑ ተረዳዱ

         ትጉ ተሰናዱ

  አጥር ሣትመዙ በትር ሣታነዱ

  ማዕዘን ሣትነቅሉ ማገር ሣትማግዱ

    ስለሕይወት ሙቀት

  ጎጆ ሣታፈርሱ መጠጊያ ሣታጡ

  የመከራን ወራት

  የጨለማን ዘመን

       እንዲ ንድታመልጡ፡፡

  እደጋማው ሃገር ተራሮች አናት ላይ በብርድ የምትኖሩ

       የደጋ ደግ ሰዎች

  አሁን ፍግ አሰጣጡ

      አዛባ አገላብጡ፡፡

  • ምንተስኖት ማሞ
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img