Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማሳደግ ተቋማት አሠራራቸውን ማስተካከል አለባቸው ተባለ

አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማሳደግ ተቋማት አሠራራቸውን ማስተካከል አለባቸው ተባለ

ቀን:

አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማሳደግ ተቋማት ቅንጅታዊ አሠራራቸውን ማዘመንና ክፍተቶቻቸውን ማስተካከል እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞች ልማት አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞች ልማት ዋና ዳይሬክተር አቶ ብሩ ወልዴ እንደተናገሩት፣ በኢትዮጵያ በርካታ ሐሳብ ያላቸው ሥራ አጥ ወጣቶች ቢኖሩም፣ እነሱን ወደ ሥራ ለማስገባት ከባንኮች የሥራ ማስኬጃ ብድር ለማመቻቸት ክፍተቶች አሉ፡፡

ወጣቶች ያላቸውን የቢዝነስ ሐሳብ በመደገፍ ለአገር ዕድገት ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው የገለጹት አቶ ብሩ፣ ባንኮችና የፋይናንስ ተቋማት ብድር ማመቻቸት እንደሚገባቸው ጠቁመዋል፡፡

የሥራ ዕድል ፈጠራን ተቀናጅቶ እንዴት መሥራት እንደሚገባ ከብሩህ ማይንድ ኮንሰልት ጋር ውይይት ማድረጋቸውንና በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም በዘርፉ ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ ያለመው ‹‹ልዩ ምልከታ›› መድረክ ሐምሌ 5 ቀን 2014 ዓ.ም. በተካሄደበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

በየዓመቱ በርካታ ወጣቶች ከዩኒቨርሲቲዎች እንደሚመረቁ የተናገሩት አቶ ብሩ፣ ከመንግሥት ተቀጣሪነት በተጨማሪ የራሳቸውን ሥራ እንዲሠሩ በተለያዩ ሁኔታ ሊታገዙ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡  

የብሩህ ማይንድ ኮንሰልት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ደሳለኝ እንደተናገሩት፣ ‹‹ልዩ ምልከታ›› በሚል የተዘጋጀው ውይይት፣ የሥራ ዕድል፣ ፖሊስና ሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚደረግ ወርኃዊ የውይይት መድረክ ነው፡፡

ነገሮች የሚታዩበት ምልከታ (ዕይታ) ባለመስተካከሉ ብዙ የተዛቡ ውጤቶች እየተገኙ መሆኑን የገለጹት አቶ ሰለሞን፣ ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር ተያይዞ ሥራ አጥነትና የወጣቶች ስደት መጨመር እንዲሁም የእርስ በርስ ጦርነት መከሰት የምልከታ (ዕይታ) ችግር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ነገሮች (ሁኔታዎች) የሚታዩበትን ዕይታ መቀየር፣ አሠራሮችን መለወጥ፣ ፖሊሲና ሕጎችን ለመፈተሽ ‹‹ልዩ ምልከታ›› የተሰኘው መድረክ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሥራ ዕድል ፈጠራ ፖሊሲና ዕቅዶችን በመፈተሽ፣ ወጣቶች እንዲደገፉና የተሻሉ ሐሳቦችን እንደተገበሩ ማድረግ የመድረኩ ዓላማ መሆኑንም አክለዋል፡፡

በእነዚህ ሥራዎች ላይ ቅንጅታዊ አሠራር እንዲኖር፣ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በሥራ ዕድል ፈጠራ በጋራ ካልሠሩ የሚፈለገውን ያህል ውጤት እንደማይገኝም አመልክተዋል፡፡

ለሥራ ዕድል ፈጠራ ባለሙያዎች ወይም ሥራ ጀማሪዎች የመነሻ ካፒታል ተደራሽነት እንዲኖር፣ ገንዘብ የማፈላለግ ሥራዎችን እንደሚሠሩም አቶ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡

አነስተኛና መካከለኛ ንግድ ሥራ ለተሰማሩ ወጣቶች የተለያዩ የብድር አማራጮችን በማፈላለግ፣ ወደ ተሻለ ከፍታ የማሻገር ሥራ መሥራት እንደማያስፈልግ፣ ባንኮች የብድር አገልግሎት የሚሰጡት ማስያዣ ለሚያቀርቡ ብቻ በመሆኑና፣ ሐሳብ ያላቸው ወጣቶች መነሻ ካፒታል ስለማያገኙ ይህን ማሻሻል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የሥራ ዕድል ፈጠራ ጉዳይ የብዙ ሚሊዮን ዜጎች ጥያቄ መሆኑን፣ የሥራ አጥነት ችግሮች፣ ድህነትንና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመቅረፍ የተቋማት በቅንጅት መሥራት ትልቅ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ካሏት 27 በመቶ ወጣቶች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሥራ አጥ መሆናቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ከኢትዮጵያ አጠቃላይ የሕዝብ ቁጥር ውስጥ ወጣቶች ቀዳሚውን ስፍራ ቢይዙም፣ እነዚህ ወጣቶች ላይ የሚታየው የሥራ ዕድል ፈጠራ ችግር አምራች እንዳይሆኑ እንዳደረጋቸውም በተለያዩ መድረኮች ሲነገር ይሰማል፡፡

‹‹ልዩ ምልከታ›› የወጣቶች ሥራና የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማበረታታት፣ ባለድርሻ አካላትን በቅርበት በመወያየት፣ የፖሊሲ ማዕቀፍ ለማሻሻል፣ ተቋማዊ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ፣ ሽርክናና አጋርነትን ለማበረታታት እንደተቋቋመ ተገልጿል፡፡ የፋይናንስ ተደራሽነትንና ከፍተኛ ጥራት ያለው የንግድ ልማት አገልግሎትን ለመስጠት የተቋቋመ የውይይት መድረክ መሆኑንም ሥራ አስፈጻሚው ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...