የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ባህል ተመራማሪው አህመድ ዘካሪያ (ረዳት ፕሮፌሰር)፣ የዘንድሮውን የዓረፋ በዓል አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ የተናገሩት፡፡ በኅብረተሰብ ሳይንስም አንፃር አንድ አካባቢ ሰላም የሚሆነው የኢኮኖሚ ዝውውሩ ጤናማ ሲሆን ነው ያሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፣ በምድርም ሆነ በሰማይ ሰላማዊ ሕይወት ለመምራት የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህልን ማጎልበት ይገባል ብለዋል፡፡ አሊያ ሰላምም ይጠፋል፣ የፈጣሪንም ትዕዛዝ አለማክበር ይሆናል ሲሉም አክለዋል። የኅብረተሰቡ የአኗኗር ሁኔታ የመቀራረቡ ነገር ጥያቄ ውስጥ መግባቱን፣ ቡና ጠጡ የሚባለው የመገናኛ ባህሉ እየደበዘዘ መምጣቱን ያወሱት ረዳት ፕሮፌሰር አህመድ፣ መቀራረብ ሲኖር ነው መረዳዳትና መተሳሰብ ሊኖር የሚችለው ሲሉ ጠቁመዋል።