Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የሰመርጃም ሬጌ ሙዚቃ ድግስ በጀርመን

ትኩስ ፅሁፎች

ከአውሮፓ ትልቁ የሚባለው የሬጌ የሙዚቃ ድግስ ሰማርጃም በጀርመን ኮሎኝ ከተማ ሰሞኑን ተካሂዷል፡፡ ዲደብሊው በድረ ገጹ እንደዘገበው፣ ከአርባ በላይ የሙዚቃ አቀንቃኞች የተሳተፉበት የዘንድሮው የ35ኛው ዓመት የሰመርጃም ሬጌ ሙዚቃ ድግስ ከተካፈሉት አንዱ

በኮሎኝ ከተማ ያደገው ጀንትልማን ነው፡፡   እ.ኤ.አ. በ2014 ወደ አዲስ አበባና ሻሸመኔ ሄዶ የሙዚቃ ሥራውን እንደሚያቀርብ በወቅቱ በፌስቡክ ገጹ ላይ ለማስተዋወቅ በለጠፈው መልዕክት «ኢትዮጵያ በጣም ታምሪያለሽ፣ ግርማዊ የተራራማ አቀማመጥ አለሽ» ሲል አወድሶ እንደነበር በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

በሁለት ትላልቅ መድረኮች ላይ በተመሳሳይ ሰዓት በቀረበው ድግስ ጀንትልማን በአንዱ መድረክ ሲገኝ፣ በሌላኛው መድረክ ላይ ደግሞ የቦብ ማርሌ ልጅ ዚጊ ማርሌ  ሲዘፍን ከመድረኩ ላይ የሚታየው ምስል ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በ1923 ዓ.ም. ሲነግሡ የነበራቸው ገጽታ (ዘውድ ደፍተው፣ ሉል ይዘውና በትረ ሥልጣን ጨብጠው) ከአንበሶች ጋር ተዛምደው ያሳይ ነበር።

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች