Monday, December 11, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

በዓረፋ ማግስት

ትኩስ ፅሁፎች

ዲቤ፣ ከበሮ፣ አታሞ፣ ጀሪካንም ቢሆን እየመቱ በዓረፋ መጨፈር ትልቅ ባሕላችን ነው። ወጣቶቻችን ለሦስት ቀናት በየሠፈራችሁ እንድትጨፍሩ ይጠበቃል። እኛ በጊዜያችን አድርገነው ለትውልዱ አስላልፈናል ይላል የባህል ሕግ ተመራማሪው አብዱልፈታህ አብደላ፣ ሐሰን ኢንጃሞ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ያወጣውን ሐተታ በማጋራት፡፡

‹‹የዓረፋ ዒድም አይደል! በባሕላችን መሠረት ዛሬ ጠዋቱ ማለዳው ላይ የሞቱ ዘመዶቻችን የሚታወሱበት ሲሆን ረፋድ ከጎረቤት ጋር የሚጨዋወቱበት ነው:: ከሰዓት ደግሞ አቧራው በጭፈራ ይጨሳል:: ከማጅራትና ከቅልጥም ሳይቀር ነጭ ላብ ይወጣል:: 3ቱ ቀናት ይቀወጥና ከዚያ ዘፈንን ወደ ካዝናው:: ሰርግ ካለ ብቻ:: ሱናው ይኸው ነው:: ዘፈን እንደ ምግብና መጠጥ ጥሩም መጥፎም አለው:: ከንግግር ጥሩና መጥፎ አለ:: ከአለባበስም እንደዚያው:: ሥርዓት ጋር ስንመጣማ ሶላትና ፆም ሳይቀር ጥሩና መጥፎ አላቸው:: በግል ስለምንጠላው ሀራም ,, በግል ስለምንወደው ፍቁድ አይኖርም::

ዱንያ ላይ መኖር ከምመርጥባቸው ነገሮች ሶላት, ከአላህ ጋር ማውራት, ጨዋታ (ቀልድ)ና የዓረፋ ዒድ ይመስሉኛል:: ዛሬ አቧራው ይጨሳል:: “ኤኒ ዋን ቱ ቢ ጭስ ካም ዖን ዊዝ  አንድር (ከበሮ)”::

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች