Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበሐምሌ ወር ነጎድጓዳማና በረዶ የቀላቀለ ዝናብ እንደሚኖር ተገለጸ

በሐምሌ ወር ነጎድጓዳማና በረዶ የቀላቀለ ዝናብ እንደሚኖር ተገለጸ

ቀን:

በሐምሌ የመጀመርያዎቹ ሳምንታት ከፍተኛ የሆነ ነጎድጓዳማና በረዶ የቀላቀለ ዝናብ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

በወሩ የሚከሰተውን የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንታኔና በውኃና በእርሻ ላይ የሚያመጣውን ተፅዕኖ አስመልክቶ እንደገለጸው፣ በተከታታይ ቀናት የሚኖረው የዝናብ መጠን ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ሊፈጥር ስለሚችል አስፈላጊው ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡

በአርብቶ አደር አካባቢዎች የሚገኘውን ውኃ በጥንቃቄ መያዝ እንደሚገባም ተጠቁሟል።

የሚፈጠረው ዝናብ ከመጠን በላይ ማሣ ላይ ውኃ እንዲተኛ ስለሚያደርግ በእርሻ እንቅስቃሴው ላይ አሉታዊ እንቅስቃሴ እንዳያስከትል የማጠንፈፊያ ቦዮችና የጎርፍ መከላከያ እርከኖች በመሥራት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም አሳስቧል።

ከመደበኛ በላይና መደበኛ ዝናብ የሚጠበቅባቸው ቦታዎች አፋር፣ አማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች መሆናቸውን፣ የብሔራዊ ኢንስቲትዩቱ የትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ጫሊ ደበሌ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በተለይም ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ ማለትም ተዳፋትና ገደላማ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ዳይሬክተሯ አሳስበዋል፡፡

የክረምቱ የዝናብ ሁኔታ በሐምሌና ነሐሴ እንደሚጠናከር የገለጹት ወ/ሮ ጫሊ፣ መብረቅ፣ ጎርፍና የበረዶ ግግር ሊኖር ስለሚችል ማኅበረሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል፡፡

ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ትቦዎችን በማፅዳትና ክፍት ማድረግ እንደሚገባም ያስገዘነቡት ዳይሬክተሯ፣ በአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለጎርፍ ተጋላጭ ተብለው በተለዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች በዘንድሮ ክረምት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በምዕራባዊ አጋማሽና በመካከለኛ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከ100 እስከ 200 ሚሊ ሊትርና በተወሰኑ ቦታዎች ደግሞ ከ200 ሚሊ ሊትር በላይ ዝናብ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

በሐምሌና ነሐሴ የክረምት ወራት በየጊዜው የሚነገረውን የአየር ትንበያ በመከታተል ማኅበረሰቡ እንቅስቃሴውን በጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡

የዓባይ፣ ባሮ-አኮቦ፣ ተከዜ፣ አዋሽ፣ ስምጥ ሸለቆ፣ ኦሞ ጊቤ፣ አፋር-ዳናከል፣ የላይኛውና መካከለኛው ዋቢ ሸበሌ እንዲሁም ገናሌ-ዳዋ ተፋሰሶች ከፍተኛ እርጥበት ይኖራቸዋል ብለዋል።

መጠነኛ እርጥበት የሚኖራቸው በታችኛው ገናሌ-ዳዋ፣ ስምጥ ሸለቆና ኦሞ-ጊቤ ተፋሰሶች እንደሆኑም ጠቁመዋል፡፡

የዝናቡ ሁኔታ በመኸር አብቃይና ዘር መዝራት ባልተጀመረባቸው አካባቢዎች የተሻለ እርጥበት ስለሚኖር ዘር ለመዝራት አመቺ መሆኑን ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

እንደ ኢንስቲትዩቱ መግለጫ፣ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይከሰትባቸዋል የተባሉት በኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች አብዛኞቹ ዞኖች፤ በአማራ፣ ትግራይ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉልና ጉሙዝ፣ ሐረሪ፣ ሲዳማና አፋር ክልል ሁሉም ዞኖች፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከምዕራብ ኦሞ በስተቀር፣ ከሱማሌ ክልል የሲቲና ፋፈን ዞኖች እንዲሁም በአዲስ አበባና ድሬዳዋ  ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...