‹‹ክብር ለጥበብ›› በሚል መሪ ቃል የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት 2ኛው አገር አቀፍ የዕውቅና እና የሽልማት መርሐ ግብር ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ ተካሂዷል፡፡ በመርሐ ግብሩም ከፊልም፣ ከሙዚቃ፣ ከዲጄ ከሥዕልና ቅርፃ ቅርፅ፣ ከሠርከስና ከኮሜዲ እንዲሁም ከጸሐፊያን ለተወጣጡና በአስተዋጽኦቸው ለላቁ 45 ባለሙያዎች ዕውቅና ተሰጥቷል፡፡ በሥነ ሥርዓቱ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳና የኪነጥበብ ሥነጥበብ የፈጠራ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ነፊሳ አልማሃዲ ተገኝተዋል፡፡ ፎቶዎቹ የሥነ ሥርዓቱን ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡