Sunday, March 3, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየ20/80 ባለ ሦስት መኝታ ቤቶች ዕጣ አለመውጣቱ ቅሬታ አስነሳ

የ20/80 ባለ ሦስት መኝታ ቤቶች ዕጣ አለመውጣቱ ቅሬታ አስነሳ

ቀን:

‹‹… የባለ ሦስት መኝታ ቤቶች ጉዳይ በቦርድ ውሳኔ ተዘግቷል››

የከተማ አስተዳደሩ

በሳምንቱ መባቻ ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በወጣው የ14ኛው ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ የ20/80 የባለ ሦስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች አለመካተታቸው ከፍተኛ ቅሬታ አስነሳ፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የከተማ አስተዳሩ 25,491 ቤቶችን ለተጠቃሚዎች በዕጣ ማስተላለፉን ተከትሎ፣ እንደ ሌሎች ቆጣቢዎች በዕጣ ቤቶችን እናገኛለን የሚል ተስፋ ሰንቀው እንደነበር ለሪፖርተር ያስታወቁት የ20/80 ባለ ሦስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች፣ ነገር ግን ባልጠበቁት ሁኔታ ከዕጣ ተሳታፊ ዝርዝር ውስጥ አለመካተታቸው ከማሳዛን አልፎ ተስፋ እንዳስቆረጣቸው ገልፀዋል፡፡

 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከንቲባ ጽሕፈት ቤት ሕጋዊ የፌስቡክ ገፅ ላይ ‹‹የባለ ሦስት መኝታ ቤት በተመለከተ ፕሮግራሙ ባለፈው ዙር በቦርድ ውሳኔ በመዘጋቱ፣ በቀጣይ በልዩ ሁኔታ የሚስተናገዱ ይሆናል፡፤›› የሚል ሐሳብ አስፍሯል፡፡

በግል ድርጀት ተቀጥረው እንደሚሠሩ የተናገሩ የ20/80 የባለ ሦስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢ የሆኑት አቶ ብሩክ ጌታቸው እንዳስታወቁት፣ ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ በወር ውስጥ ከሚያገኙት ገቢ በመቀነስ ያለማቋረጥ ሲቆጥቡ መቆያታቸውን ተናግረው፣ አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት እሳቸውና መሰል የባለ ሦስት መኝታ ቤት አማራጭ ተመዝጋቢዎች ከ14ኛው ዙር የዕጣ ዝርዝር ውጭ መሆናቸው ፍትሐዊ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተገቢውን ቁጠባ ወር ጠብቀው ሲፈጽሙ መቆየታቸውን የተናገሩት ስማቸውን እንዳይገለጽ የጠየቁ ሌላ አስተያየት ሰጪ የዚህ ዙር ተሳታፊ ባለመሆናቸው፣ ተስፋ ከማስቆረጥ አልፎ ከዚህ በኋላ ቤት አገኛለሁ የሚል እምነታቸውን እንደሸረሸረ ገልጸዋል፡፡

አቶ ብሩክ እንዳስታወቁት፣ ከገቢያቸው ጋር ያልተመጣጠነው የቤት ኪራይ ወጪ በየዕለቱ ከሚስተዋለው የዋጋ ንረት ጋር ተዳምሮ በዚህ ወቅት ለቤት ባለቤትነት የሚያደርጉትን የመቆጠብ አቅም ሁሉ እየተገዳደረው ይገኛል ብለዋል፡፡ የቤት ዕድለኛ ከሚሆኑበት አጋጣሚ ውጭ መሆናቸው ተገቢ አለመሆንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በ14ኛው ዙር ለዕጣ ከቀረቡት ቤቶች ለ20/80 ቤት ልማት ፕሮግራም የአንድ ካሬ ማስተላለፊያ ዋጋ 7,997.17 ብር ሲሆን፣ ይህም በ13ኛው ዙር ከነበረው የ4,511.27 ብር ዋጋ የ77.2 በመቶ የዋጋ ጭማሪ የተደረገበት ነው፡፡

በዚህ ዙር የወጡ የ40/60 ቤት ልማት ፕሮግራም የአንድ ካሬ ዋጋ 11,162.97 ብር ሲሆን፣ ይህም በ13ኛው ዙር ከነበረው የ6,922.14 ዋጋ የ61.2 በመቶ የዋጋ ጭማሪ የታየበት ነው፡፡ ያም ሆኖ በዚህ ዙር የቀረበው የአንድ ካሬ ሜትር ዋጋ በግል አልሚዎች ከሚገነቡ ቤቶች ዋጋ አኳያ በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

በ14ኛው ዙር ዕጣ አወጣጥ ብቁ ናችሁ የተባሉ በ20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም 27,195 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም 52,599 በአጠቃላይ 79,794 ተመዝጋቢዎች በዕጣ ድልድሉ መካተታቸው ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የ14ኛው ዙር የጋራ መኖሪያ ቤት ዕድለኞች ዕጣ ከመውጣቱ በፊት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ የቤት ልማት ፕሮግራም ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በ17 ዓመታት ውስጥ ለኅብረተሰቡ ማቅረብ የተቻለው 300 ሺሕ ያህል ቤቶችን ብቻ መሆኑን ገልጸው፣ አሁንም በሚወጡት ውስን ቁጥር ያላቸው ቤቶች የኅብረተሰቡን ችግር መቅረፍ ስለማይችሉ፣ ከተማ አስተዳደሩ አምስት ዓይነት የቤት ልማት አማራጮችን መዘርጋቱን ተናግረዋል፡፡

ከእነዚህም አመራጮች ውስጥ በመኖርያ ኅብረት ሥራ ማኅበር፣ በመንግሥትና በግል ባለሀብቶች አጋርነት፣ የመኖርያ ቤት በሽርክና ማቅረብ፣ የግል አልሚዎች በማበረታታት እንዲሁም የቁጠባ ቤቶችን ገንብቶ በተመጣጣኝ ኪራይ ማቅረብም የሚሉት ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...