Tuesday, September 26, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ራሚስ ባንክ አቶ ዓሊ አህመድ ዓሊን የባንኩ ፕሬዚዳንት አድርጎ ሰየመ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ፈቃድ ያገኘውና በቅርቡም ወደ ሥራ ይገባል ተብሎ የሚጠበቀው ራሚስ ባንክ አክሲዮን ማኅበር አቶ ዓሊ አህመድ ዓሊን የባንኩ ፕሬዚዳንት አድርጎ ሰየመ፡፡

ከባንኩ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመላክተው አቶ አሊ የባንኩ ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ የተሾሙ ሲሆን፣ ሹመታቸውም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቀርቦ የጸደቀ በመሆኑ ሥራቸውን ጀምረዋል፡፡

አቶ ዓሊ በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከ22 ዓመታት በላይ ያገለገሉ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በአዋሽ ባንክ ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ያገለገሉ መሆናቸውም ይጠቀሳል።

በትምህርት ዝግጅታቸውም ከኖርዊች ዩኒቨርሲቲ በኢንተርናሽናል ቢዝነስ ኤምቢኤ ዲግሪ፣ በማኔጅመንትና በቢዝነስ አስተዳደር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢኤ ዲግሪ እንዳላቸው ተገልጿል፡፡ 

ራሚስ ባንክ በኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ሦስተኛው ባንክ በመሆን ገበያውን እንደሚቀላቀል የሚጠበቅ ሲሆን በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ላይ 50 ቅርንጫፎችን በመክፈት ሥራ ይጀምራል ተብሏል፡፡

የባንክ አገልግሎቱን ለመጀመር የሚያስችል ፈቃድ ከብሔራዊ ባንክ ያገኘው ራሚስ ባንክ የአገሪቱን የባንክ ኢንዱስትሪ የሚቀላቀለው በ757.5 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታልና ከ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ የተፈረመ ካፒታል በመያዝ እንደሆነ ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ የባንኩ ባለአክሲዮኖች ብዛትም 8,614 መሆኑን መረጃው ያመለክታል።

በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ወስደው ወደ ሥራ የገቡት ዘምዘምና ሒጅራ ባንኮች ሲሆኑ ራሚስ ደግሞ ሦስተኛው ከወለድ ነፃ ባንክ ይሆናል፡፡ 

ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ከሚሰጡ ባንኮች ሌላ በአሁኑ ወቅት በመስኮት ደረጃ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ባንኮች ቁጥር 13 ደርሷል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች