Monday, May 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልየመጀመርያው የፈላስፋ ሰማዕት ሕይወትና ፍልስፍናው አስተምህሮ

የመጀመርያው የፈላስፋ ሰማዕት ሕይወትና ፍልስፍናው አስተምህሮ

ቀን:

የካፑቺን ፍራንቸስካና የፍልስፍና እና የነገረ መለኮት ተቋም የፍልስፍና መምህሩ ፀሓዬ ይኄይስ ለንባብ ካበቋቸው ሦስት መጻሕፍት አንዱ ‹‹ዝኽረ ሶቅራጠስ›› ይባላል፡፡ አዘጋጁ በመግቢያቸው ላይ እንደገለጹት፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቃለሉትና የተቀሩት ሌሎች የፕሌቶ ጽሑፎች ከ2300 ዓመታት በፊት የተጻፉ ናቸው፡፡ ይህም ሆኖ ከተጻፉበት ዘመን ጀምሮ በጥንታዊው፣ በመካከለኛው፣ በህዳሴውና በዘመናችንም አስተሳሰብ በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ተፅዕኖዋቸው ሊያሳርፉ የቻሉ ዘመን ያልሻራቸው ዕፁብ ድንቅ ጽሑፎች ናቸው፡፡ በሁሉም ሊባል በሚችል መልኩ ይብዛም ይነስም፣ እግረ መንገድም ይሁን በዋነኝነት፣ በከፊልም ይሁን በሙላት ያልተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች የሉም ሊባል ቢቻልም የስህበት ማዕከላቸው ግን መለኮታዊ ያልሆነ ግን ደግሞ ወደ ቁስ አካላዊ ተፈጥሮም ያልወረደ የሰው ልጅ አዕምሮአዊ ተፈጥሮ ማለትም አመክንዮ – logos ነው፡፡

‹‹በፕሌቶ አጋፋሪነት የተመራው ጥንታዊው የግሪክ ሥነ – ዕውቀታዊ እመርታ በሰው ልጅ አዕምሮአዊ ተፈጥሮና ሥነ አመክንዮ በኩል እስካሁን ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ግልጽነትን ፈጥሯል፡፡ ፕሌቶ በዕውቀት ረገድ ከመደበኛ ትምህርት በመለስ የጊዜው ሥነ ዕውቀታዊ ከፍታ ጠንቅቆ በመረዳት ራሱን ከፍ ወዳለ ሥፍራ ያሸጋገረ ሊቅ ነበር፡፡ የጽሑፎቹ ይዘትና ቅርፅ በጨረፍታ ያስተዋለ አንባቢ ለዚህ አባባላችን ምስክር ከመሆን አያንስም፡፡ በተመኩሮም ቢሆን አድማሱ ለማስፋት ምስክር መሆን አያንስም፡፡ በተመኩሮም ቢሆን አድማሱ ለማስፋት የሚያስችለውን ያህል ራሱን አደራጅቷል፡፡ የተወለደው በ428 ዓመተ ዓለም አካባቢ ነው፡፡ የሞተውም በ80 ዓመቱ በ348 ዓመተ ዓለም አካባቢ ነው፡፡››

በዚህ መጽሐፍ ተጠቃለው የተተረጉሙት አራት ጽሑፎች ማለትም ዩቲፔሮ፣ አፖሎጂ፣ ክሪቶና ፌዶ እንግዲህ በረዥሙ የፍልስፍና ታሪክ በአጠቃላይ፣ በምዕራባውያን የፍልስፍና ታሪክ ደግሞ በተለየ የለውጥ ነጥብ አኑረዋል ተብለው ከሚታመንባቸው በውጤቱም በአያሌው ከሚወደሱና ከሚሞገሱ ፈላስፎች አንዱ በሆነው በዚህ ግሪካዊ ፈላስፋ የተጻፉ ናቸው፡፡ ይሁንና ይዘታቸው ስለ ጸሐፊው ሕይወት አሊያም ፍልስፍና የሚያንፀባርቁ አይደሉም (የሐሳብ መወራረሱ ሳይዘነጋ)፡፡ በነዚህ አራት ጽሑፎች ፕሌቶ የሶቅራጠስን የመጨረሻዎቹ አሳዛኝ መዋዕል ከፍልስፍናዊ ዕሳቤዎቹ ጋር በማስተዛዘል ይተርካል ሲሉም ያክላሉ፡፡

- Advertisement -

አራቱን ዓበይት ጽሑፎችንም እንደሚከተለው አብራርተዋል፡፡

‹‹ዩቲፔሮ የክሱን ዋናው ጭብጥ ለማሰማት በንጉሥ አርኮን በረንዳ ፊት ለፊት በተገኘው ሶቅራጠስና አንድ ወላጅ አባቱን በግድያ ወንጀል ከሶ በዚያው በተገኘው የሥነ መለኮት ሊቅ መካከል የተደረገ ምልልስ ነው፡፡ ኦፖሎጂ ሶቅራጠስ በችሎት ፊት ቀርቦ ራሱን የተከላከለበት፣ የሞት ፍርዱን ተከትሎ ሌላ የቅጣት አማራጭ ያቀረበበት፣ በመጨረሻም ፍርዱ እንደ ፀና ጥቂት የመሰነባበቻ መልዕክት ያስተላለፈበት ጽሑፍ ነው፡፡ ክሪቶ ሶቅራጠስ የሞት ፍርዱን በሚጠባበቅበት ጊዜ በእስር ቤት ውስጥ ከረዥም ጊዜ ወዳጁ ጋር የሚያደርገው ምክክርና ክርክር ያትታል፡፡ ፌዶ ሶቅራጠስ ከጓደኞቹና አባሪ ተባባሪዎቹ ጋር ስለተለያዩ ፍልስፍናዊ ርዕሰ ጉዳዮች የሚከራከሩበትና በመጨረሻም የመርዝ ጽዋውን ተጎንጭቶ ለመጨረሻ ጊዜ ያንቀላፋበትን አሳዛኝ አጋጣሚ ምስል ካሳች ታሪክ የያዘ ነው፡፡

የፕሌቶ ጽሑፎች በአጠቃላይ በእነዚህ አራት ጽሑፎች ደግሞ በተለይ ሶቅራጠስ የተባለ ፈላስፋ በዋና ገጸ ባህሪነት በማሳተፍ የሚያናግርባቸው ናቸው፡፡ ይህም በምሁራን መካከል ለዘመናት የዘለቀ (አሁንም የተቋጨ የማይመስል) ጥያቄ አስከትሏል፡፡ በአንድ በኩል በፕሌቶ ጽሑፎች የተገለጸው ሶቅራጠስና መዋዕሉ ተዓማኒነታቸው ምን ያህል ነው? የሚል ጥያቄ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በሶቅራጠስ አፈ ቀላጤነት የተነገሩ ፍልስፍናዊ አስተምሮዎች በትክክል የሶቅራጠስ ዕሳቤዎች ናቸው፣ ወይስ ፕሌቶ ሶቅራጠስን በቃለ አቀባይነት በመጠቀም የሚነግረን የገዛ ራሱ ዕሳቤዎች ናቸው? የሚሉ ናቸው፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች ለምንና እንዴት ተነሱ ብለን ስንጠይቅ ከአያሌ ምክንያቶች አንዱና ምናልባትም ዋነኛው ሶቅራጠስ የተባለው ስለመዋዕሉም ይሁን ፍልስፍናዊ ትምህርቱ በቀለም ከትቦ ያስተላለፈው ምስክርነት ባለመኖሩ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...