Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትሊጠናቀቅ ዘጠና ደቂቃ በቀረው ፕሪሚየር ሊግ የሚያሸንፈው ቅዱስ ጊዮርጊስ ወይስ ፋሲል ከነማ?

ሊጠናቀቅ ዘጠና ደቂቃ በቀረው ፕሪሚየር ሊግ የሚያሸንፈው ቅዱስ ጊዮርጊስ ወይስ ፋሲል ከነማ?

ቀን:

በተለያዩ ከተሞች ለ29 ሳምንታት ሲከናወን የቆየው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ፣ የውድድር ዘመኑ ሊጠናቀቅ የዘጠና ደቂቃ ዕድሜ ብቻ በቀረበት በዚህ ወቅት ባለድሉን ለመለየት አልተቻለም፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ 30ኛ ሳምንት የመዝጊያ መርሐ ግብሩ የአሸናፊነት ክብሩን የሚያጣጥመው፣ ያለፈው ዓመት ሻምፒዮኑ ፋሲል ከነማ፣ አልያም የ14 ጊዜ ሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚለው የሚታወጅበት ዋዜማ ላይ ይገኛል፡፡

ለወትሮው በተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ተግዳሮቶች ሲታማ የነበረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ፣ ካለፈው የውድድር ዓመት ጀምሮ በዲኤስ ቲቪ አማካይነት በቀጥታ ሥርጭት መተላለፉን ተከትሎ ብዙ ነገሮቹ ተሻሽለዋል፡፡ ፕሪሚየር ሊጉ ላለፉት ሁለት አሠርታት ከእግር ኳሳዊ ባህሪው ይልቅ የውዝግብ መንስዔ ሆኖ ለከፍተኛ የንብረትና መሰል ጉዳቶች ምክንያት ሆኖ መቆየቱ የሚዘነጋ አይደለም፡፡

ፕሪሚየር ሊጉ በክለቦች ባለቤትነት እንዲካሄድ የተወጠነው ከ1999 ዓ.ም. ጀምሮ ሲሆን ከዓመታት ውጣ ውረድ በኋላ ነው ክለቦች ሊጉን በባለቤትነት እንዲያስተዳድሩ ሕጋዊ ዕውቅናን ያገኙት ደግሞ በ2012 ዓ.ም. ነው፡፡

- Advertisement -

ከ2013 የውድድር ዓመት ጀምሮ በተወሰኑ ከተሞች የቴሌቪዥን ቀጥታ ሥርጭት ኖሮት ሲከናወን የቆየው ሊጉ ቡድኖች የልፋታቸውን ውጤት በችሎታቸው ብቻ ማግኘት መጀመራቸው ብዙዎች የሚጋሩት እውነት ሆኗል፡፡

በሐዋሳ፣ በድሬዳዋና በአዳማ እንዲሁም የመጨረሻው መርሐ ግብሩን በባህር ዳር ስታዲየም እያከናወነ የሚገኘው የዘንድሮ ፕሪሚየር ሊግ፣ ውድድሩ ሊጠናቀቅ አንድ ሳምንት ብቻ በቀረበት በአሁኑ ወቅት ሦስተኛውን ወራጅ ቡድን እንዲሁም አሸናፊውን ቡድን ለመለየት የአንድ ጨዋታ ውጤት መለያ የሆነው ዘጠና ደቂቃን መጠበቅ ግድ ብሏል፡፡

የውድድሩ አሸናፊ ለመሆን በአንድ ነጥብ ብቻ ተበላልጠው ቀሪውን አንድ ጨዋታ በጉጉት እንዲጠበቅ ያደረጉት ፋሲል ከነማ ከድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም አንጋፋው ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ ከአዲስ አበባ ከተማ ከነገ በስቲያ ዓርብ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

ክለቦቹ ቀደም ሲል በወጣላቸው ፕሮግራም መሠረት ይጫወቱ ወይስ በሌሎች አገሮች እንደሚታወቀው በተለያየ ስታዲየም በተመሳሳይ ሰዓት ይጫወቱ የሚለውን ለመለየት ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 22 ቀን 2014 ዓ.ም. የሊግ ካምፓኒው የቦርድ አመራሮች፣ የውድድርና
ሥነ ሥርዓት ኮሚቴውና አራቱ ክለቦች በተገኙበት ውሳኔ እንደሚሰጥበት የሊግ ካምፓኒው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ከጅማ አባ ጅፋርና ሰበታ ከተማ ቀጥሎ ወደ ታችኛው ሊግ የሚወርደው አንዱ ቡድን አልታወቀም፡፡ የመውረድ ዕጣ ይገጥማቸዋል ተብለው የሚጠበቁት ሦስቱ ቡድኖች ማለትም አዲስ አበባ ከተማ፣ አዳማ ከተማና ድሬዳዋ ከተማ ሲሆኑ፣ አንድ አንድ ጨዋታ እየቀራቸው አዲስ አበባ ከተማና አዳማ ከተማ እኩል 32 ነጥብ ላይ ሲገኙ፣ ድሬዳዋ ከተማ ደግሞ 30 ነጥብ ይዟል፣ ወራጁን አንድ ቡድን ለመለየት እንደ ሻምፒዮኑ ሁሉ የመጨረሻው የጨዋታ መርሐ ግብር ይጠበቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...