Monday, May 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትበሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስና ፋሲል ከነማ ለዋንጫው ተፋጠዋል

በሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስና ፋሲል ከነማ ለዋንጫው ተፋጠዋል

ቀን:

በባህር ዳር ስታዲየም እየተከናወነ የሚገኘው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ከፍተኛ ፉክክር እየታየበት ይገኛል፡፡ ወትሮ በአንድ ክለብ የበላይነት ብቻ ተይዞ በመጠናቀቅ የሚታወቀው ሊጉ፣ በፉክክር ከታጀበ ሰንባብቷል፡፡ ዓርብ ሰኔ 17 ቀን 2014 ዓ.ም. 28ኛ ሳምንት ጨዋታን ተከትሎ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስና ፋሲል ከተማ ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ ጠቧል፡፡

የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን በበላይነት ማንሳት የቻለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ለዓመታት ከዋንጫ መራቁን ተከትሎ፣ የዘንድሮን ዋንጫ የማንሳት ዕድል እንዳለው ቢነገርም፣ ፋሲል እያሳየ በመጣው ወጥ አቋም ከመሪው ጋር ያለውን ነጥብ ማጥበብ ችሏል፡፡ በዚህም ለሻምፒዮናነት ተስፋ እንዲሰንቅ አስችሎታል፡፡

የዓምናው ሻምፒዮና ፋሲል ከነማ አምስት ጨዋታዎች በተከታታይ በማሸነፍ፣ በ28 ጨዋታ 58 ነጥብ ሰብስቦ ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡ በአንፃሩ ቅዱስ ጊዮርጊስ ባለፉት አምስት ጨዋታዎች ሁለት አሸነፎ፣ ሁለት አቻ ወጥቶና በአንዱ በመረታት በ59 ነጥብ አንደኛ ደረጃ ተቀምጧል፡፡

- Advertisement -

ጥሩ ስብስብ ያለውና በአሠልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ እየተመራ የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ያልነበረውን አቋም በዚህ ዓመት ማሳየት ችሎ ነበር፡፡ ሆኖም ባለፉት አምስት ጨዋታዎች ያሳየው እንቅስቃሴ ለዋንጫ እያደረገ ያለውን ግስጋሴ ገትቶታል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ28ኛ ሳምንት ከሐዲያ ሆሳዕና ጋር ባደገው ጨዋታ አቻ መውጣቱ፣ ከፋሲል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ አውርዶታል፡፡

ሁለቱ ክለቦች ካላቸው ነጥብ አንፃር ቀሪዎቹ ሁለት ጨዋታዎች የበለጠ ተጠባቂ ሆነዋል፡፡

በዚህም መሠረት በ29ኛ ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ አርባ ምንጭን ሲገጥም፣ ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ሊጉን በሻምፒዮናነት የሚያጠናቅቀውን ክለብ ለመለየት ፍንጭ ይሰጣል፡፡

የሊጉን የመጨረሻ ጨዋታ በ30ኛ ሳምንት ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ አበባን ሲገጥም ፋሲል ድሬዳዋን ይገጥማል፡፡ ይኼም ጨዋታ ሁለቱ ክለቦች የሚያደርጉትን ፍጥጫ የሚለይ ይሆናል፡፡

በዘንድሮ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከሚታየው ፉክክር ባሻገር ደግሞ፣ በወራጅ ቀጣና ላይ ያሉት ክለቦች ውጤት ትኩረትን ስቧል፡፡ በሊግ ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ የሚገኙት ድሬዳዋ፣ ጅማና ሰበታ ከተማ ጥሩ ጊዜ እያሳለፉ አይገኙም፡፡ ድሬዳዋ በ29 ነጥብ 14ኛ፣ ጅማ አባ ጅፋር በ23 ነጥብ 15ኛ እንዲሁም ሰበታ ከተማ በ21 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዘው ዕድሜያቸው በሊጉ ለመቆየት እየታተሩ ይገኛሉ፡፡

በተለይ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መሳተፍ ከጀመረ ጀምሮ በተፎካካሪነቱ የሚታወቀው አዳማ ከተማ፣ በወራጅ ቀጣና ውስጥ መገኘቱ አግራሞትን ፈጥሯል፡፡ ምንም እንኳን ክለቡ የገንዘብ ቀውስ አጋጥሞት ቢቆይም፣ በሒደት ችግሩን ቢቀርፍም በሊጉ ግን ውጤታማ መሆን አልቻለም፡፡

ሊጉ ራሱን በራሱ ማስተዳደር ከጀመረ በኋላ ከቴሊቪዥን የሚያገኘው ገቢ እንዲሁም የስፖንሰርሺፕ ስምምነቱ እየጨመረ ቢመጣም፣ ለተጫዋቾች ደመወዝ መክፈል የተሳናቸው ክለቦች ተበራክተው ነበር፡፡

በዘንድሮ ውድድር የሰበታ፣ የጅማና የአዲስ አበባ ተጫዋቾች ደመወዝ አልተከፈለንም በሚል ቅሬታቸውን በደብዳቤ ሲገልጹ ከርመዋል፡፡ በዚህም ወትሮንም የመንግሥት ካዝና ላይ የተንጠለጠሉት የክልል ክለቦች ችግር በገንዘብ ዕጥረት ሲመቱ ውጤታቸው ላይ ቀውስ ለመፈጠሩ በዋና ምክንያትነት ይጠቀሳል፡፡  

ምንም እንኳን ክለቦች የሚያደርጉት ጨዋታ በዲኤስቲቪ የመተላለፍ ዕድል ቢኖረውም፣ ክለቦች ግን ከተለያዩ ተቋማት ጋር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ማሰር የሚያስችላቸው አጋጣሚ መጠቀም አለመቻላቸው የገንዘብ ችግራቸውን ሊፈቱ አለማስቻሉ ይነገራል፡፡

በክልሎች ሲከናወን የቆየው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2014 ዓ.ም. ውድድር ከሁለት ሳምንት በኋላ በባህር ዳር ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...