Tuesday, May 21, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ጣሊያን ለአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በአነስተኛ ወለድ 22 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ሰጠች

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

ጣሊያን ለአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በአነስተኛ ወለድ ለድጋፍ የሚውል 22 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ሰጠች፡፡ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴና የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ተፈራርመዋል።

ብድሩ በዋነኝነት በተለይ ለቡልቡላ፣ ለቡሬ፣ ለይርጋለምና ለባአከር የተቀናጀ የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተገልጿል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ስምምነቱ በተፈረመበት ወቅት እንደገለጹት፣ ከጣሊያን መንግሥት የተገኘው ብድር የገጠር ትራንስፎርሜሽን ማዕከላትን በመደገፍ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የአርሶ አደሮችን ገቢ ለማሳደግ፣ ወደ ውጭ ከሚላኩ ምርቶች የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ያግዛል።

በተጨማሪም ከውጭ የሚመጡ የተቀነባበሩ ምግቦችን ለመተካት ጠቃሚ እንደሚሆነ አክለዋል።

በምግብ ማቀነባበር ዘርፍ የተሰማሩ የግል ድርጅቶችም ወደ ኢንዱስትሪ ፓርክ ገብተው እንዲሠሩ ለመደገፍ ብድሩ ያግዛል ያሉት ሚኒስትሩ፣ በአምራቾችና በአርሶ አደሮች መካከል ባለው ግንኙነት ላይ በማተኮር በቴክኖሎጂ የታገዘ አሠራር ለማስፋፋት ይውላል ብለዋል።

የክልሎችን የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች አቅምና ለልህቀት ማዕከላት ግንባታና ለተገነቡትም መሣሪያዎች ማሟያ እንደሚውል፣ በተጨማሪም ለተመረጡ የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች የብድር አገልግሎት ለመስጠት ይረዳል ሲሉ አስረድተዋል።

‹‹የግል አምራች ድርጅቶችም ወደ ተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው በአገር ውስጥና በውጭ ያላቸውን የገበያ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የሚችሉበትን ዕድል ለመፍጠር እንጠቀምበታለን፤›› በማለት አቶ አህመድ አብራርተዋል።

 የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ በበኩላቸው፣ የብድር ስምምነቱ ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን አጋርነት ለማጠናከር እንደምትፈልግ ያሳያል ብለዋል።

በአግሮ ኢንዱስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በአስተዳደርና ስደትን በመቀነስ በኩል ጣሊያን ለኢትዮጵያ ድጋፍ እንደምታድርግ ተናግረዋል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች