Tuesday, May 21, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ለዓመታት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያና ናይጀሪያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሄደ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

በየሁለት ዓመት ይካሄድ የነበረው የኢትዮ-ናይጄሪያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በኮሮና ወረርሽንና በሁለቱ አገሮች የተለያዩ የውስጥ ጉዳዮች ምክንያት ከአምስት ዓመት በኋላ እንደገና ለሦስተኛ ጊዜ ከሰኔ 6 እስከ ሰኔ 7 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

የትዮጵያና ናይጄሪያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን የተመሠረተው እ.ኤ.አ. በ2006 በአዲስ አበባ በተካሄደ የመጀመሪያ ስብሰባ ሲሆን፣ ሁለተኛው የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ደግሞ በ2017 በናይጄሪያ አቡጃ ከ11 ዓመት በኋላ ነበር የተዘጋጀው፡፡

ይህ ለሦስተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ የተካሄደው ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከአንድ ሳምንት በፊት በናይጄሪያ ያደረጉኑትን የሥራ ጉብኝት ተከትሎ ነው፡፡

ሁለቱ አገሮች በመጀመሪያ በአዲስ አበባ ባካሄዱት የጋራ የሚኒስተሮች ስብሰባ  በጤና፣ በኢንዱስትሪ፣ በግብርናና በባህል ዘርፍ አብሮ ለመሥራት ተስማምተው የነበረ ቢሆንም ስብሰባው በተያዘለት ጊዜ በየሁለት ዓመቱ መካሄድ አለመቻሉንና ሁለቱ አገሮች ባሉባቸው ክፍተቶች ምክንያት መሠራት የነበረባቸው ጉዳዮች አለመከናወናቸውን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምዕራብ አፍሪካ አገሮች ዳይሬክተር ኤልያስ መላኩ (አምባሳደር) ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በጋራ ኮሚሽኑ አማካይነት እ.ኤ.አ. በ2006 የ30 ዓመት አጠቃላይ 20  ስምምነቶች ተካሂደው የነበሩ ቢሆንም፣ እስካሁን አፈጻጸሙ በሚጠበቀው ደረጃ አለመካሄዱንና ይህን አፈጻጸም ሊከታተል የሚችል ኮሚቴ እንዲቋቋም ከኢትዮጵያ በኩል ጥያቄ መቅረቡን አክለው ገልጸዋል፡፡

የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን የተቋቋመው በአገሪቱ መካከል ያለውን የግንኙነት እንቅስቃሴ የተሻለ ግንኙነት መሠረት አድርጎ ቢሆንም እስካሁን ወደሚፈለገው ደረጃ ማሳደግ አለመቻሉን አብራርተዋል፡፡

በኢትጵያ ከ14 ያልበለጡ ባለሀብቶች እንዳሉ የጠቀሱት (አምባሳደር) አሁን ላይ በሁለቱ አገሮች የሚታየውን ወደ ፖለቲካና ዲፕሎማሲ ብቻ ያደላ የሚመስለውን ግንኙነት በቀጣይ ጉዳዩን በመከታተል በሁለቱ አገሮች መካከል የተሻለ የኢኮኖሚና ኢንቨስትመንት ተጠቃሚነትን ማምጣት ላይ ይሠራል ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት በቆየው የጋራ ኮሚሽኖች ስብሰባ በስታስትቲክስ፣ ኢንዱስተሪያል ፖሊሲ መረጃና ልምድ ልውውጥ፣ በጥቃቅንና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ጥምረት በመፍጠር የልምድ ልውውጥ ስለሚደረጉባቸው ጉዳዮች፣ በግልና መንግሥት አጋርነት ሊሠሩ ስለሚችለባቸው እንዲሁም ወታደራዊ ጉዳዮች የተካተቱበት አምስት ተጨማሪ ዘርፎች ላይ አብረው ለመሥራት መስማማታቸውን በኢትዮጵያ የናይጀሪያ አምባሳደር ቪክቶር አደንኩሌ ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ አገሮች የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን የቀጣይ ስብሰባ እ.ኤ.አ. በ2024 በናይጄሪያ አቡጃ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች